ታህሣስ 2፣2017
‘’አካል ጉዳተኞችን ለማገዝ በሚል ተመስርተው የለግል ጥቅም የሚሰሩ ማህበራት አሉ’’ ሲል የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ተናገረ፡፡
የተለያዩ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችን ለመደገፍ የተመሰረቱና መልካም የሚባል ስራ የሚሰሩ ማህበራት ቢኖሩም በአካል ጉዳተኞች ስም ተመስረተው የግለሰቦች ጥቅም ማግኛ የሆኑ ማህበራት እንዳሉ ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝደንት ወይንሸት ግርማ(ዶ/ር) ‘’በአካል ጉዳተኞች ስም ድርጅት አቋቁመው እንደ ንግድ የሚሰሩ አሉ’’ ብለዋል፡፡
በእንዲህ አይነት ተግባራት የተሰማሩ ማህበራትን ለማጥራት የኦዲት ፍተሻ ሊደረግቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ይህም የመንግስት ሀላፊነት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
Comments