መጋቢት 2 2017
በሰላም እጦት ከዚያም ደግሞ በድርቅ ሲፈተን የቆየው የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በ2016 ዓ.ም የክረምት ወቅት ባጋጠመው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያትም ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ወጥተዋል ተባለ፡፡
በዞኑ ባሳለፍነው የክረምት ወቅት ባጋጠመ የበረዶ እና የመሬት መንሸራተት በተለይ ሁለት ወረዳዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ከ40 ሺ በላይ የሚሆን ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው ወጥተዋል ያለው ዞኑ የኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡
በሁለቱ ወረዳዎችም ያሉ ማሳዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ጉዳት ደርሶበታል የተባለ ሲሆን ዞኑ ባደረገው ጥናትም ነዋሪው ለመፈናቀል እና ለከፍተኛ ችግር ተዳርጓል ተብሏል፡፡
አምራቾች ናቸው ከሚባሉ የዞኑ አካባቢዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት እነዚህ ሁለቱ ወረዳዎች በተያዘው አመት ግን አምራቾቹ ከዚህ ቀደም ሲከውኑት የነበረውን ስራ እየሰሩ አይደለም፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments