00:00
መጋቢት 24 2017
ከ863 የሂሳብ ባለሞያዎችና ኦዲተሮች 824ቱ ያቀረቡለት የሂሳብ ሰነድ የተጭበረበረ መሆኑን ገቢ አሰብሳቢው ቢሮ ተናገረ፡፡
ከበድ ያለ ማጭበር ውስጥ የገቡት 334ቱ ባለሞያዎች ፈቃዳቸው እንዲነጠቅም ጠይቋል፡፡
የሂሳብ መዝገቦች የቅድመ ኦዲት ስራ መከወኑን የሚናገረው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በዚህም ወቅት ባለፈው ዓመት ብቻ 36,729 የታክስ መዝገቦች ገቢ በማሳነስና በመሰወር የሚቀርቡ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
በእነዚህ የተጭበረበሩ ሰነዶች ምክንያት ሊሰበስበው የተገባ የነበረ ከ10.6ቢሊዮን ብር በላይ ሳይሰበስብ መቅረቱን ነግሮናል፡፡
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሂሳብ እና የኦዲት ቦርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው 863 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች 824ቱ ባለሙያዎች ከባለሃብቶች ጋር በመመሳጠር ገቢያቸውን በማሳነስና በመሰወር ለገቢ ሰብሳቢው ቢሮ ያቀረቡ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
Comments
00:00