ሚያዝያ 17 2017
ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ ወጪ፤ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችን ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡
በቢልና ሚሊናዳ ጌትስ ፋውንዴስን በተገኘ የ14.3 ሚሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ የምንዛሪ ተመን ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጤና ሚኒስቴርና በኤምኤስአይ #MSI ኢትዮጵያ የሚተገበር ነው፡፡
ለ4 ዓመታት ይተገባራል በተባለው ፕሮጀክቱ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በሲዳማ ክልሎች አማራጭ የጤና አገልግሎት፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚሰጥበት መሆኑን በMSI ሪፕሮዳክቲቭ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አበበ ሽብሩ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡
በፕሮጀክቱ በእነዚህ አራቱ ክልሎች ውስጥ ባሉ 230 የመንግስት የጤና ተቋማት አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የነገሩን ዶክተር አበበ በአንድ በኩል የጤና ባለሞያዎቹን አቅም በማጎልበት፤ በሌላ በኩል ምንም አይነት የጤና አገልግሎት በሌለባቸው ቦታዎች በ6 ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድኖች የተጠቀሱትን የጤና አገልግሎቶች እንደሚሰጡም አስረድተዋል፡፡
Comments