የግብር ዕዳ እያለባቸው ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆኑ 62 ግለሰቦች ያፈሩትን ሃብት ላለባቸው እዳ ማካካሻ እንደሚያውለው የገቢዎች ቢሮ ተናግሯል
TRACK

የግብር ዕዳ እያለባቸው ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆኑ 62 ግለሰቦች ያፈሩትን ሃብት ላለባቸው እዳ ማካካሻ እንደሚያውለው የገቢዎች ቢሮ ተናግሯል

00:00

የካቲት 28 2017

የግብር ዕዳ እያለባቸው ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆኑ 62 ግለሰቦች ያፈሩትን ሃብት ላለባቸው እዳ ማካካሻ እንደሚያውለው የገቢዎች ቢሮ ተናግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከፋይናንስ ኢንቴሌጀንስ አስተዳደር ጋር በመሆን የግብር እዳቸውን ያልከፈሉኝን ግለሰቦችና ተቋማት እያደንኩ ነው ሲል በተደጋጋሚ ሲናገር ቆይቷል፡፡

ካለፈው ዓመት ጀምሮ ሳይከፈል ከተከማቸው ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ እዳ ከ6.4ቢሊዮን ብር በላዩን በዚህ ዓመት በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ አስከፍያለሁ የሚለው ቢሮው፤ ቀሪውን 4.6 ቢሊዮን ብር የግብር እዳ ያልከፈሉኝን የማደኑ ስራ እንደቀጠለ ነው ብሏል፡፡

ካልተከፈለው ውስጥ 3.2 ቢሊዮን ብሩን ያልከፈሉት 62 ግለሰቦች ናቸው፤ በተደጋጋሚ እዳቸውን እንዲከፍሉ ጥሪ ቢደረግላቸውም ሊከፍሉ ባለመቻላቸው ከሃገር እንዳይወጡ ታግደዋል፡፡

Comments

00:00