የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርሳቸው የሚገበያዩት ከአጠቃላይ ግብይታቸው ከ15 በመቶ ያልበለጠ ነው፡፡
ሌላው ወደ አሜሪካ አውሮፓ እሲያ የሚደረግ ግብይት ነው፡፡
ደካማ የሆነውን የእርስ በእርስ ግብይታቸውን ለማሳደግ ፣ ምርትም እንደልብ በአፍሪካ ሀገራት እንዲሸጥ ያስችላል የተባለለት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ስምምነት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ አመታት ተቆጠሯል፡፡
ኢትዮጵያም 5 ሺህ 800 በላይ የሌሎች ሀገራት ምርቶች ያለ ቀረጥ ወደ ሀገሯ ገብተው እንዲሸጡ ተስማምታለች፡፡
ስምምነቱ እሷም በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ምርቶቿን ከቀረጥ ነፃ መሸጥ ያስችላታል፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ከአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ተጠቃሚ መሆን ትችል ይሆን?
Comments