ህዳር 26፣2017
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነጻ ለማድረግ በሚል በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠት ከጀመረ 3 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
በእነዚህ 3 ዓመታት ብቻ የ12ኛ ከፍል ፈተናን ከተፈተኑት መካከል በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን በላይ ነው፡፡
ለመሆኑ እነዚህ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች የት ናቸው? በምንስ እንዲሰማሩ እድሎች ተመቻቹላቸው?
ትምህርት ሚኒስቴር እና በፓርላማ ጉዳዩን የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ አባልን ጠይቀናል፡፡
ታደሰ በዛ(ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ በሞያቸውም መምህር ናቸው፡፡
ታደሰ (ዶ/ር) ብሔራዊ ፈተናን ለማያልፉት ተማሪዎች የተለያዩ እድሎች ሊመቻችላቸው ይገባል ያሉን ሲሆን ይህ የማድረግ ሀላፊነት ደግሞ በዋናነት የትምህርት ሚኒስቴር እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
የአቅም ማሻሻያ መርሀግብር(Remedial Program) መጀመሩን ያበረታቱት የቋሚ ኮሚቴው አባል፤ ነገር ግን ተጨማሪ እድሎች ተፈጥረው እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ ማድረግ ይገባልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፍቅሩ አምባቸው
Comments