ህዳር 26፣2017
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከአለም አቀፉ ኩባንያ ከማስተር ካርድ ጋር በመስማማት ለደንበኞቹ ‘’ንብ የቅድመ ክፍያ ካርድ አገልግሎት’’ መጀመሩ ተሰማ።
ባንኩ ለደንበኞቹ በየትኛውም የአለም ማእዘን ለንግድ ቢዝነስ ጤና ቱሪዝምና ሌሎችም አገልግሎቶች ሲጓዙ ይህ የቅድመ ክፍያ ካርድ እንደሚያገለግላቸው ተናግሯል።
ደንበኞች ከጉዞና ከዕለት ተዕለት ወጪዎች ባለፈ ለኢንተርኔት ኦንላይን ግብይት እና ከጉዞ ጋር ለተያያዙ ግብይቶች በቀላሉ ክፍያ እንዲፈጽሙና ሌሎች ብርቱ ጉዳዮችንም እንደሚያቀልላቸው የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ለሸገር ሬድዮ ነግረዋል።
ካርዱ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውና ንብ ኢንተርናሽናል ባንክም በሁሉም ቅርንጫፎቹ ለደንበኞቹ ስነወዱ እንደሚያደርገው ተሰምቷል።
የቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ ለባንኩ ደንበኞች በአለም አቀፍ ንግድ ውስጥ እንዲሳተፉ ያግዛቸዋል ተብሏል።
Comments