TRACK
በጋሞ ዞን ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡
00:00
መጋቢት 7/2018
በጋሞ ዞን ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡
የቀሪዎቹን አስከሬን ለማውጣት ሲደረግ የቆየው በቁፋሮ የታገዘ የማፈላለግ ስራም እንዲቆም መደረጉን ሰምተናል፡፡
ይህን ያለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ነው።
እንደ ቢሮው መረጃ ከሆነ አስከሬን የማፈላለግ ስራው ቆሞ የ44 ሰዎች አስከሬን አደጋው በተከሰተበት በዚያው ስፍራ የቀብር ቦታው ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል ተብሏል፡፡
Comments
00:00