በተመድ በአለም አቀፍ ደረጃ 2026 የአርብቶ አደር እና የግጦሽ መሬት ዓመት እንዲሆን በተወሰነው መሰረት አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ መደረጉ ተሰማ፡፡
TRACK

በተመድ በአለም አቀፍ ደረጃ 2026 የአርብቶ አደር እና የግጦሽ መሬት ዓመት እንዲሆን በተወሰነው መሰረት አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ መደረጉ ተሰማ፡፡

Avatar

ጥር 19/2018

የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የአየር ጠባይ ለውጥንም ለመቋቋም ይረዳል ተብሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ 2026 የአርብቶ አደር እና የግጦሽ መሬት ዓመት እንዲሆን በተወሰነው መሰረት አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ መደረጉ ተሰማ፡፡

ከግብርና ሚኒስቴር ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላም እና ፀጥታ ኢንስቲትዩ ጋር በመተባበር የመንግስታቱ ድርጅት በወሰነው መሰረት በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ምሁራንና የአርብቶ አደሮች መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከ12 እስከ 15 በመቶ የሚደርሱ የማህበረሰብ አባላት አርብቶ አደር መሆናቸው የሚነገር ሲሆን ኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ድርሻ አላቸውም ተብሏል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሚሊዮን በላይ አርብቶ አደሮች መኖራቸው የሚናገሩት የፓስቶራሊስት ፎረም ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ተዘራ ጌታሁን ዋናው ትኩረቱ የአየር ጠባይ ለውጥ ችግርን መከላከልና በምግብ እህል እራስን ለመቻል ለሚደረገው ትግል የአርብቶ አደር የእንስሳትና የግጦሽ መሬት ጉዳይ ቀዳሚው ነው ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

የኔነህ ሲሳይ

Comments

Avatar