ሚያዝያ 17/2018
ከወረቀት አሰራር፤ ከፊት ለፊት ተገናኝቶ ከመስራት ያልተላቀቀው የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ዲጅታላይዜሽን አለመቀየሩ ቋሚ ተገልጋይ ደንበኞቹን እያሳጣው ነው ተባለ፡፡
ቴክኖሎጅን ታግዞ አገልግሎት መስጠት የማይችል ከሆነ ዘፉር ችግር ላይ መውደቁ እንደማይቀር የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ባለሙያዎቹ ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ዲጅታላይዜሽን እና የደንበኛ ታማኝነት ያላቸው ግንኙነት በሚል በቀረበ ጥናት ላይ ነው፡፡
የኢንሹራንስ ዘርፉ እስካሁን ለደንበኞቹ አገልግሎት ለመስጠትም ሆነ ሌሎች ስራዎቹን የሚከውነው ቴክኖሎጅን ተጠቅሞ ባለመሆኑ መስራት በሚገባው ልክ እንዳይሰራ እና ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡
Comments