ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው?
TRACK

ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው?

Avatar

ጥቅምት 21 2018

ከ3 ዓመታት ወዲህ የሚታየው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ላይ ያሳደረው የስነ ልቦና ጫና ተስፋ እስከመቁረጥ የደረሰባቸው መሆኑን ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተማሪው፣ በትምህርት ባለሞያው እንዲሁም በተማሪ ቤተሰቦች ቅሬታ እያስነሳ ነው፡፡

ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው አመለካከት ምን መሳይ ነው? ስንል በጠየቅንበት ወቅት ቤተሰብ ልጆቻቸው እንዲማሩላቸው ስለሚፈልጉ አልያም አልተማሩም ላለመባል ብቻ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ሀሳብ የሰማነው ከዘንድሮ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ነው፡፡

ተማሪዎቹ አሁን ላይ ለትምህርት ስላላቸው ፍላጎት እና እያስተናገዱት ስላለው ስሜት ምን ይጠቁመናል? ስንል ባለሞያ አነጋግረናል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እቅድ እና ስራ አመራር ትምህርት ክፍል ባልደረባ ዶክተር ደሞዜ ደገፋ አሁን እየታየ ያለው የ12ተኛ ክፍል ውጤት መውረድ በትምህርት ላይ ያሉትን ተማሪዎች የመማር ፍላጎታቸው እንዲቀንስ እና ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋቸዋል ይላሉ።

የፈተና ውጤቱ ችግር መኖሩን አሳይቷል የሚሉት ደሞዜ(ዶ/ር) ተማሪው ይኮርጅ ነበር የሚለው ላይ ብቻ ከማተኮር በአግባቡ የሚማሩበት ሁኔታ አለ ወይ? ብቁ መምህራን አሉ ወይ? የሚለው መፈተሽ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Comments

Avatar