ኢሰመኮ በህክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የስራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት እንዳይሆኑ ትኩረት ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ
TRACK

ኢሰመኮ በህክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የስራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት እንዳይሆኑ ትኩረት ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ

Avatar

ግንቦት 14 2017

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በህክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የስራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት እንዳይሆኑ ትኩረት ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ፡፡

መንግስት ለችግሩ ግልፅና ዘላቂ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ሲልም አሳስቧል፡፡

ኮሚሽኑ የህክምና ባለሙያዎች እያደረጉት ካለው የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ባለሙያዎች ስለመኖራቸውም አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የአያያዝ ሁኔታቸውንም ክትትል እያደረግሁበት ነው ሲል በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡

ባለሙያዎቹ በተወካያቸው በኩል ተመጣጣኝ ደሞዝ እያገኘን አይደለም በሚልና ከጥቅማ ጥቅም ፣ ከሙያ እድገትና የተለያዩ እድሎች ፣ ከምቹ የስራ ቦታ የስራ ቦታ ነፃነት ጋር የተያዙ ጥያቄዎችን ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለጤና ሚኒስቴር ያቀረቡ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡

የተጠቀሱትንና ሌሎችም 12 ጥያቄዎች በተሰጠው የ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ባለማግኘታቸውም ካለፈው ግንቦት 5 ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውንም ተረድቻለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፡፡

Comments

Avatar