በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡
TRACK

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡

00:00

ሚያዝያ 20 2017

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡

ይህም በገጠር ያሉ ዜጎች ዳቦ ወይም ሌላ የሚፈልጉት ምርትን ለመግዛት ወደ ከተማ እንዳይወጡ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ ያሉ ወረዳዎች በየአካቢያቸው እንደሚያገኙት የግብዓት ዓይነት እያንዳንዳቸው እስከ 3 ኢንዱስትሪዎች እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተናግሯል፡፡

በዚህም ባለፉት 9 ወራት 206 ኢንዱስትሪዎች በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች መቋቋማቸው የተቀሰው ተቋሙ ቁጥራቸውን ለማሳደግ በብርቱ መስራቴን እቀጥላለሁ ብሏል፡፡

በገጠር አካባቢዎች ኢንዱስተሪዎች ማስፋፋት የአካባቢው ነዋሪዎች ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪየም የስራ እድል በመፍጠር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ይቀንሳል ሲባል ሰምተናል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በንጋት መኮንን

Comments

00:00