በምርት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት አንድ እንቁላል እስከ 25 ብር እንዲሸጥ እድል ፈጥሯል ተብሏል
TRACK

በምርት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት አንድ እንቁላል እስከ 25 ብር እንዲሸጥ እድል ፈጥሯል ተብሏል

Avatar

ሰኔ 18 2017

በዶሮ እርባታ ላይ የተሰማሩ ትናንሽ አርቢሮች ከዘርፉ መውጣታቸው ለእንቁላል መወደድ ምክንያት ሆኗል ተባለ።

አርቢዎቹ ከዘርፉ እንዲወጡ ያስገደዳቸውም የመኖ ዋጋ ውድነት እንደሆነ ሰምተናል።

መኖ አቅራቢ ፋብሪካዎችም ቢሆኑ በጥሬ እቃ እጥረት እና መወደድ ምክንያት እየተቸገሩ መሆኑን ሰምተናል።

በዚህ እና በሌሎች ተደራራቢ ምክንያቶች የእንቁላል መኖ ዋጋ ከፍ ማለቱን ተነግሯል።

አንድ ኩንታል የእንቁላል ጣይ የዶሮ መኖ ከሁለት ወር በፊት ሲሸጥ ከነበረው 4,800 ብር አሁን 5,800 ብር እየተሸጠ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በተለይ አቅም የሌላቸው ትናንሽ አርቢዎች እየተቸገሩ በመምጣታቸው ከገበያው ለመውጣት ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን በምርት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት አንድ እንቁላል እስከ 25 ብር እንዲሸጥ እድል ፈጥሯል ተብሏል።

Comments

Avatar