መስከረም 23 2018
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በአለም ጤና ድርጅት ተመዝኖ አንድ ደረጃ ማሻሻሏ ተነገረ፡፡
ኢትዮጵያ በአለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ምደባ(Classification) ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ (ደረጃ 3) ላይ መድረሷ ተነግሯል፡፡
ይህ እውቅና የበዙ ጠቀሜታዎች ያሉት እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን እና ጤና ሚኒስቴር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ አስረድተዋል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት ኦዲተሮች በስምንት ተግባራት ላይ የሰነድ ግምገማ ተደረጎ ጥሩ የሚባል አፈፃጸም በማግኘታቸው ነው ይህ እውቅና የተገኘው ሲሉ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) በመድረኩ ተናግረዋል፡፡
ይህ ውጤትም ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት፤ ለሕብረተሰቡ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ውጤታማ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የህክምና ምርቶችን ለማቅረብ የሚረዳው እና የሚያበረታው እንደሆነም የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ መድሀኒት የምትቆጣጠርበት ስርዓቷ በህዝብ አመኔታ እንዲኖረው ይህ እውቅና እንደሚረዳም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
Comments