የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በያመቱ ለ500 ሕፃናት ህክምና እያደረገ ቢሆንም ከህመሙ ጋር በአመት 25 ሺህ ህፃናት ስለሚወለዱ የውጭ ተቋማትንም እርዳታ እፈልጋለሁ ብሏል፡፡
ለህክምና የሚመጡልኝ ህፃናት ቁርጥም ከአቅሜ በላይ ነው ፤ የጤና ባለሙያ እጥረትም አለብኝ ብሏል፡፡
የማዕከሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ በኢትዮጵያ በየአመቱ በተፈጥሮ ከ25 ሺህ በላይ ህፃናት እንደሚወለዱ በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
ህክምናውና የሐኪሞች ቁጥር በዛው ልክ ስላልሆነ ፈተና እየገጠመን ነው ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ህክምናው ከፍተኛ ሀብት የሚፈለግ መሆኑንም በመጥቀስ የሁሉንም ድጋፍ ይፈልጋል ብለዋል፡፡
ወንድሙ ሀይሉ
Comments