''ኢትዮጵያ በአሜሪካ የ10 በመቶ ቀረጥ ብቻ እንድትከፍል ከተወሰነባቸው ሃገራት መካከል መሆኗ የውጭ ባለበሀብቶችን እንድትስብ መንገድ ከፍቷል''
TRACK

''ኢትዮጵያ በአሜሪካ የ10 በመቶ ቀረጥ ብቻ እንድትከፍል ከተወሰነባቸው ሃገራት መካከል መሆኗ የውጭ ባለበሀብቶችን እንድትስብ መንገድ ከፍቷል''

Avatar

ሚያዝያ 28 2017

ኢትዮጵያ በአሜሪካ አነስተኛ የተባለው የ10 በመቶ ቀረጥ ብቻ እንድትከፍል ከተወሰነባቸው ሃገራት መካከል መሆኗ የውጭ ባለበሀብቶችን እንድትስብ መንገድ ከፍቷል ሲል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ፡፡

ከሰሞኑ እንኳን ከጃፓን፣ ከቬትናም፣ ከቻይና እና ከህንድ የመጡ ባለሃብቶች በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ ገብተው ለመስራት የቅድመ ኢንቨስትመንት ምልከታ ማድረጋቸው ተጠቅሳል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ አሜሪካ ምርቶቻቸውን በሚልኩ 100 ሀገራት ላይ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ላይ የተጣለው ታሪፍ 10 በመቶ ሲሆን በሁሉም ሀገራት ላይ የጣሉት የመነሻ ታሪፍ ወይም #Baseline_Tariff እንደሆነ ተመልክቷል።

ታሪፉ በአሜሪካ የሚገኙ ገዥዎች ለኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው ፍላጎት እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል በማለት የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች መናገራቸው ይታወሳል።

በዚያው አንጻር አስር በመቶ መሆኑ ለኢትዮጵያ በጎ ጎን ሊኖረው ይችላልም ብለዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንም ትራምፕ በሌሎች ሀገራት የጣሉት ከፍተኛ ታሪፍ፤ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት እየጨመረው ነው ብለዋል፡፡

Comments

Avatar