ግንቦት 15 2017
በኢትዮጵያ አራት ሚሊዮን ተማሪዎችን ማሰልጠን የሚችሉ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት እንዳሉ ይነገራል፡፡
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ በመምጣቱ ወደ ቴክኒክና ሞያ ትምህርት ቤት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጎታል ተብሏል፡፡
አቶ ገላና ወ/ሚካኤል በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊ ናቸው፡፡
እርሳቸው እንደሚሉት እንደ ሃገር ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ተማሪዎች እጅግ አስፈላጊ ናቸው ብለዋል፡፡
ሆኖም ከቴክኒክና ሞያ ተቋማት ሰልጥነው የሚወጡ ተማሪዎች አያስፈልጉም ማለት እንዳልሆነና የተሻለ የደመወዝ ተከፋይ እነሱ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡
Comments