ሰኔ 18 2017
#ምጣኔ_ሐብት
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያው፤ ሽያጭ ልዋጩ በሶስት የተከፈለ ነው።
አንደኛው መደበኛው በባንኮች የሚከናወነው የየእለት ምንዛሪ ገበያ ነው።
ሁለተኛው ፍቃድ ያገኙት ስድስቱ የግል የውጭ ምንዛሪ ገዥ እና ሻጭ የፎርኤክስ ቢሮዎች ናቸው።
ሦስተኛው በጥቁር ኢኮኖሚ አንገት ለአንገት የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ገበያን በመረበሽ ተያይዞ የነበረው የትይዩ የውጭ ምንዛሪ በረንዳ ነው።
ሐገር ይህን ለማስታገስ ብላ በማዕከላዊ ባንክ በየጊዜው የሚደረገው ጥብቅ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርና መመሪያ እያወጣ እየተገበረ ነው።
በእርግጥ ለትርፍ የተቋቋሙት ባንኮች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እዳ እና ጫና ቢኖርባቸውም እንዴት በውጭ ምንዛሪ ሽያጭና ግዥ ትርፋቸው ከፍተኛ ይሆናል ተብለው ይተቻሉ።
የማዕከላዊ ባንኩን ጥብቅ አሰራር እና የብር የመግዛት አቅም ውሳኔ ተከትሎ አርጩሜውን ላለመቅመስም ወደኋላ ሲሉ ይታያል።
Comments