የት/ት ስራ ውስብስብ እና የብዙ ወገኖች ጥንካሬ የሚጠይቅ ነው ተባለ፡፡
TRACK

የት/ት ስራ ውስብስብ እና የብዙ ወገኖች ጥንካሬ የሚጠይቅ ነው ተባለ፡፡

Avatar

መስከረም 13 2018

የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውጤታማ ለማድረግ እና ብቁ ተማሪዎችን ለማብዛት በአንድ ተቋም ብቻ የሚከናወን አይደለም፤ የት/ት ስራ ውስብስብ እና የብዙ ወገኖች ጥንካሬ የሚጠይቅ ነው ተባለ፡፡

በአሜሪካን ሀገር ከ45 ዓመታት በላይ በት/ት ስራ ላይ የተሰማሩትና በአሁኑ ወቅት ዶ/ር ነጋ የት/ት ማዕከል በሚል በኦንላይን ት/ት የሚሰጡት ዶ/ር ነጋ ወርቁ የት/ት ሥርዓትን ለማዘመን የሁሉም ባለድርሻ ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ተማሪን ለማስተማር የትምህርት ሥርዓቱ እና ካሪኩለሙ ብቻውን በት/ት ሚኒስቴር በኩል የሚፈፀም አይደለም የሚሉት ባለሞያው ወላጆችን ጨምሮ የበርካታ ባለድርሻዎችን ድጋፍ ይፈልጋል ብለዋል፡፡

Comments

Avatar