የኢትዮጵያ መንግስት የአደጋ ስጋት አለ ብሎ በየዓመቱ ከሚለያቸው 5 ነጥቦች መካከል በሰው የመነገድ ወንጀል አንዱ እና ዋነኛው ነው ተባለ
TRACK

የኢትዮጵያ መንግስት የአደጋ ስጋት አለ ብሎ በየዓመቱ ከሚለያቸው 5 ነጥቦች መካከል በሰው የመነገድ ወንጀል አንዱ እና ዋነኛው ነው ተባለ

00:00

ሐምሌ 25 2017

የኢትዮጵያ መንግስት የአደጋ ስጋት አለ ብሎ በየዓመቱ ከሚለያቸው 5 ነጥቦች መካከል በሰው የመነገድ ወንጀል አንዱ እና ዋነኛው ነው ተባለ፡፡

በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ የሚሰራው በሰው የመነገድ ወንጀል አለም አቀፍ ባህሪ ያለው ጭምር በመሆኑ ከሀገራት ጋር ከፍተኛ ትብብር በመፍጠር እየተሰራ ነው ሲሉ የነገሩን የፀረ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ፅ/ቤት ሀላፊው አብርሃም አያሌው ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ዋና ዋና የብሔራዊ ደህንነት ስጋት አጀንዳ ብሎ ከለያቸው 5 ነጥቦች መሀከል አንዱ በሰዎች የመነገድ ወንጀል ነው ሲሉ አቶ አብርሃም ተናግረዋል፡፡

Comments

00:00