በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደው ሰፈራ መሬት ከወሰዱ ባለሀብቶች እስከ 75 በመቶው ወደ ልማት ሲገቡ አይታይም፡፡
TRACK

በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደው ሰፈራ መሬት ከወሰዱ ባለሀብቶች እስከ 75 በመቶው ወደ ልማት ሲገቡ አይታይም፡፡

Avatar

ህዳር 25 2018

በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደው ሰፈራ መሬት ከወሰዱ ባለሀብቶች እስከ 75 በመቶው ወደ ልማት ሲገቡ አይታይም፡፡

መሬቱ ላይ ለመስራት ሳይሆን በተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ፈቃድ የባንክ ብድር ለማግኘት አልመው ወደዚህ ስራ የሚገቡ አሉ ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ 7,000 የሚሆኑ ባለሃብቶች በእርሻ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት 2.2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ክልሎች መውሰዳቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ባለሃብቶቹ መሬቱን የወሰዱት ለገበያ የሚውሉ የተለያዩ ሰብሎችን ለማምረት እንደሆነ መረጃው ያመለክታል።

ለግብርና ኢንቨስትመንት ከተሰጠው 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት እስከ አሁን ባለሃብቶቹ የለማው ግን 25 በመቶው ብቻ እንደሆነ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል።

Comments

Avatar