የካንሰር ህክምና የሚውሉ መድሃኒቶች በዋጋም ውድ በመሆናቸው የሚፈጠረውን እጥረት ለመፍታት ድጎማ እየተደረገ እየቀረበ ነው ተባለ
TRACK

የካንሰር ህክምና የሚውሉ መድሃኒቶች በዋጋም ውድ በመሆናቸው የሚፈጠረውን እጥረት ለመፍታት ድጎማ እየተደረገ እየቀረበ ነው ተባለ

00:00

ነሐሴ 13፣2016

ለካንሰር ህክምና የሚውሉ መድሃኒቶች በኢትዮጵያ በቂ አቅራቢ አለመኖሩና በዋጋም ውድ በመሆናቸው የሚፈጠረውን እጥረት ለመፍታት ድጎማ እየተደረገ እየቀረበ ነው ተባለ፡፡

በ2016 በጀት ከ106 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ #የካንሰር_ህክምና ለሚሰጡ የህክምና ማዕከላት መከፋፈሉ ተነግሯል፡፡

ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት እንደሰማነው በአገልግሎቱ በአጠቃላይ 1020 #የህክምና_ግብአት እና መድሃኒቶች እንደሚቀርቡና ከእነዚህም ውስጥ ከመድሃኒቶች ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ከሚሸመት ወጪ ድጎማ ተደርጎቸውና ከአለም አቀፍ ለጋሾች ድጋፍ የሚቀርቡ እንደሚገኙበት የነገሩን የአገልግሎቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አወል ሀሰን ናቸው፡፡

Comments

00:00