00:00
ሐምሌ 30፣2016
ለህዳሴው ግድብ ግንባታ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሰበሰበው ገቢ በሃገር ውስጥ በሚሰበሰበው በ6 እጥፍ ያነሰ ነው ተባለ፡፡
ምንም ዓይነት የውጭ ብርድም ይሁን እርዳታ ሳይጠየቅበት እየተገነባ ላለው የህዳሴ ግድብ ከህዝቡ በ2016 ዓ.ም ዓመት ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
ከዚህ ውስጥ አብላጫውን ድርሻ የሚይዘው(1 ብሊዮን ብር ያህሉ) የተሰበሰበው ከሃገር ውስጥ የቦንድ ሽያጭና ስጦታ ነው፡፡
ዓመቱ ሲጀመር 2 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ እንደተነሳ የሚናገሩት የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ሃይሉ አብርሃም ከ70 በመቶ በላዩን ማሳካት ተችሏል ይላሉ፡፡
ግንባታው እየተጠናቀቀ ያለው የህዳሴ ግድብ የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን አስመልክቶ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
Comments
00:00