ተሻሽሎ የተሰናዳው የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቀቅ አዋጅ ሁለት ጊዜ የብቃት ምዘና ወስደው ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ከስራ እንዲሰናበቱ ይደነግጋል
TRACK

ተሻሽሎ የተሰናዳው የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቀቅ አዋጅ ሁለት ጊዜ የብቃት ምዘና ወስደው ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ከስራ እንዲሰናበቱ ይደነግጋል

Avatar

ሰኔ 5፣ 2016

ተሻሽሎ የተሰናዳው የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቀቅ አዋጅ ሁለት ጊዜ የብቃት ምዘና ወስደው ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ከስራ እንዲሰናበቱ ይደነግጋል፡፡

ይሁንና ምዘናው ገለልተኝነቱ የተጠበቀ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ይነሳበታል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የብቃት ምዘናን ጨምሮ የተለያዩ የማሻሻያ ድንጋጌዎች እንዲታከሉበት ተጠይቋል፡፡

በረቂቅ ሕጉ ላይ ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ውይይት ተካሄዷል፡፡

በህጉ ሊካተቱ እና ግልፅ ሊሆኑ ይገባል ተብለው ከተነሱ ነጥቦች መካከል

• የመንግስት ሰራተኛው ለቤት ኪራይ እና ለትራንስፖርት ተብሎ የሚሰጣቸው ጥቅማ ጥቅም ላይ ዳግም ታክስ መክፈል የለባቸውም፡፡

• የሰራተኞች ምዘና በትውውቅ እና በብሔር መጠቃቀሚያ እንዳይሆን ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ስለሚካሄዱ የሚረጋገጥበት ዘዴ መኖር አበለት፡፡

• ሲቪል ሰርቪሱ ብሔር ብሔረሰቦችን ይምሰል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ የኮሚሽኑ አቋም ምንድነው?

• እንደ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ላሉ ተቋማት ህጉ ከፊል ነፃነት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

Comments

Avatar