የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል?
TRACK

የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል?

00:00

ጥቅምት 5 2018

የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ትናንት በተጀመረው እና እስከ ነገ በሚቀጥለው ጉባኤ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች፣ ባህርተኞች እና ቀጣሪ ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው፡፡

ለመሆኑ ይህ ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል ስንል የኢትዮጰያ ማሪታይም ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋን ጠይቀናቸዋል፡፡

ጉባኤው በዘርፉ ለሚሰለጥኑ ባለሞያዎች የገበያ ትስስር፣ ለማሰልጠኛ ተቋማት ደግሞ ዘርፉ የሚፈልገውን አለም አቀፍ ክህሎት ምን መሳይ ነው የሚለው እንዲያውቁት እንዲሁም ከትልልቅ የዘርፉ ድርጅቶች ልምድ ለመውሰድ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል ሀላፊው፡፡

ኢትዮጵያ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢኒስትቲዩት እና በቢሾፍቱ የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይም አካዳሚ ባህርተኞችን እያሰለጠነች ነው ተብሏል፡፡

በእነዚህ ማሰልጠኛዎች የሚሰለጥኑት ባለሞያዎች የሚበዙት የሚቀጠሩት በዓለም ዓቀፍ ተቋማት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

Comments

00:00