በሀይማኖት ተቋማት እና በንጹሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንደሚያወግዝ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተናገረ
TRACK

በሀይማኖት ተቋማት እና በንጹሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንደሚያወግዝ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተናገረ

Avatar

የካቲት 25፣2016

በሀይማኖት ተቋማት እና በንጹሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አወገዘ፡፡

ችግሮች በንግግር እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል፡፡

‘’ንጹሀን የፖለቲካ ማወራረጃ ሊሆኑ አይገባም’’ ያለው ጉባኤው ‘’ተገቢ የሆነ ጥበቃ እና ከለላ ሊደረግላቸው ይገባል’’ ሲልም ተናግሯል፡፡

አሁን ላይ በየእምነት ተቋማት እና በንጹሀን ላይ የሚደርሰውን ሞትና ጉዳት ‘’ኢ ፍትሃዊ ነው’’ ብሎታል፡፡

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ‘’ሁሉም በየእራሱ መንገድ መሄዱ፣ በመደማመጥና በመነጋገር የሚያምኑ ጥቂቶች መሆናቸው፤ ግጭቶች ጎልተው እንዲታዩ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ናቸው’’ ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ #የንፁሀን_ሞት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar