የንብረት ታክስ ትመና የከተሞችን ዓመታዊ ወጪ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰላ ነው ተባለ
TRACK

የንብረት ታክስ ትመና የከተሞችን ዓመታዊ ወጪ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰላ ነው ተባለ

Avatar

ታህሳስ 17፣2017

የንብረት ታክስ ትመና የከተሞችን ዓመታዊ ወጪ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰላ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተደረገ ውይይት ወቅት ነው፡፡

የንብረት ታክስ ከሌሎች የታክስ ዓይነቶች የሚለየው ግብር ከፋዩ ይህን ያህል መክፈል እችላለሁ ብሎ የሚያቀርበው ሳይሆን በከተሞች ውሳኔ ተተምኖ ሚሰበሰብ ነው ተብሏል፡፡

ረቂቁ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መመሪያ ኃላፊ አቶ ተወዳጅ መሃመድ ናቸው፡፡

የንብረት ታክስ በሊዝ ይዞታ በሚተዳደር መሬት የሚጠቀም መብት ላይ በቤት በህንፃ እንዲሁም በመሬት ማሻሻያ ላይ የሚጣል እንደሆነ አቶ ተወዳጅ አስረድተዋል፡፡

Comments

Avatar