ከ45 የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 250 ወጣቶች በአዲስ አበባ ይገኛሉ
TRACK

ከ45 የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 250 ወጣቶች በአዲስ አበባ ይገኛሉ

Avatar

ጥቅምት 4፣2017

ከ45 የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 250 ወጣቶች በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡

ወጣቶቹ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ስለ አህጉሪቱ የሥርዓተ ምግብ ለመነጋገር ነው፡፡

ተፈጥሮ ላይ መሰረቱን ያደረገ የምግብ ልዓላዊነት ላይ ለመምከር ወጣቶቹ ተሰባስበዋል፡፡

ፕሮግራሙን ያሰናዳው ደግሞ በምግብ ሉአላዊነት ላይ የሚሰራው Alliance for food sovereignty in Africa (AFSA) የተባለ ተቋም ነው፡፡

በምግብ እጦት፣ በተመጣነ ምግብ ችግር ውስጥ ያለችው አፍሪካ ይህንን ችግር በሀገር በቀል እውቀት ታግዛ ምርት እንድታመርት፣ የሌላው አለም ማዳበሪያ፣ መድሃኒትም ሆነ ምርጥ ዘር ጥገኛ እንዳትሆን መላ ማበጀት የአዲስ አበባ የAFSA ጉባኤ አጀንዳ ነው፡፡

የገበሬ ሀገሯ ኢትዮጵያ ግብርናዋ እንደ እድሜውና እንደሚያስተዳድረው ህዝብ ብዛት ሊያድግ አልቻለም፡፡

ግብርናው ከበሬ ትከሻ፣ ከሞፈር እና ቀንበር አልተላቀቀም፡፡

የአብዛኛው የአፍሪካ ሀገር የግብርና ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡

Comments

Avatar