ህዳር 30፣2017
በኢትዮጵያ በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ከሚገኝ ሰዎች መካከል ከ81,000 በላዩ የት እንዳሉና ጤናቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አይታወቅም ተባለ፡፡
ይህ የተባለው በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባሳለፍነው 2016 ዓ.ም በተካሄደውና ኢትዮጵያ በቫይረሱ ስርጭት ምን ደረጃ ላይ እንደሆነች ለማወቅ በተካሄደው ጥናታዊ ትንበያ ነው፡፡
በኢንስቲትዩቱ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 605,238 በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ( #HIV_AIDS) በደማቸው ይገኛል፡፡
ከእነዚህ መካከል 523,683ቱ ህክምና አግኝተው የፀረ ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ ይገኛል፤ ቀሪዎቹ 81,555 የቫይረሱ ተጠቂዎች እንደሆኑ ይታወቅ እንጂ ወደ ህክምናም ይሁን መድሃኒት እያገኙ እንዳልሆነ ኢንስቲትዩቱ ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡
በኤችአይቪ ኤድስ ዙሪያ ከሚሰሩ ተቋማት መካከል የሆነው AIDS HEALTH CARE FOUNDATION (AHF) የተባለውን ግብረ ሰናይ ድርጅት ስለ ጉዳዩ ጠይቀናል፡፡
ምንታምር ፀጋው ያሰናዳችውን በማርታ በቀለ
Comments