''የውጭ ምንዛሪን ወደ ኢትዮጵያ በሰከንዶች ለተላከለት ደንበኛ እንዲደርስ የሚያስችል አዲስ ቴክኖኖሎጂ አሰናድቻለሁ'' የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
TRACK

''የውጭ ምንዛሪን ወደ ኢትዮጵያ በሰከንዶች ለተላከለት ደንበኛ እንዲደርስ የሚያስችል አዲስ ቴክኖኖሎጂ አሰናድቻለሁ'' የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ

Avatar

መስከረም 24፣2017

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ምንዛሪን ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ በአነስተኛ የመላኪያ ዋጋ እና በሰከንዶች ገንዘቡ ለተላከለት ደንበኛ እንዲደርስ የሚያስችል አዲስ ቴክኖኖሎጂ አሰናድቻለሁ ሲል የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተናገረ፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በአነስተኛ የመላኪያ ዋጋ እና በቅፅበት ለተቀባይ እንዲደርስ በብሎክ ቼን ቴክኖሎጂ የታገዘ የሬሚታንስ(የሀዋላ) አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቴን ጨርሼ ወደ ስራ ገብቻለሁ ብሏል፡፡

ባንኩ አገልግሎቱን የሚሰጠው በአለም አቀፍ ደረጃ በአካታች ፋይናንስና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ከሚሰራው InFTF ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ነው የተባለ ሲሆን ወጭ ቆጣቢ፣ ቀላል እና ተደራሽ ነው ተብሏል።

በአፍሪካ ቴክኖሎጂውን መጠቀም የጀመረው የመጀመሪያው ባንክ ነው የተባለው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከዚህ ቀደም በሀዋላ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ይፈታል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ከዚህ በፊት በሀዋላ ከውጭ የሚላከው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ ገንዘብ ካልሆነ መላክ እንደማይችል የተነገረ ሲሆን አሁን ባንኩ ወደ ስራ ያስገባው ቴክኖሎጂ ግን ከ1 ዶላር ጀምሮ መላክ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

Comments

Avatar