00:00
ጥቅምት 19፣2017
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ጥያቄ አስነሳ፡፡
የሚሾሙ ሚኒስትሮች ከተማሩት ትምህርት ጋር የተቀራረበ ተቋም እንዲመሩ ተጠይቋል፡፡
በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት የቀድሞው የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ለሞያው ምን ያህል ቅርብ እንደሆኑ ተጠይቋል፡፡
ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የተባሉ የእንደራሴ ምክር ቤት አባል ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በህግ ሞያቸው በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ዘርዝረው ይሁንና በውጭ ጉዳይ ላይ ያላቸው የስራ ልምድ ቢገለጽ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምክንያቱም ከዲፕሎማሲ አንጻር እኛ ያለንበት ቀጠና ከአባይ ጋር ከባህር በር ጋር ተያይዞ ብዙ ጫናዎች አሉብን ያሉት የምክር ቤት አባሉ በመስኩ ላይ ብዙ ልምድ ያላቸው ሰዎች እንደሚያሰፈልጉ ይታመናል ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለዚህ የታጩበት ሌላ ያላየነው ነገር ካለ ቢነገረን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
Comments
00:00