ታህሳስ 16፣2017
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አለመረጋጋት ይታያል፡፡
በዚህም ምክንያት ከአንድ ዓመት እስከ ሶስት ዓመት የመማር ማስተማር የተቋረጠባቸው አካባዎች መኖራውም ይታወቃል፡፡
በጦርነት ቀጠና ውስጥ የነበሩ አንዳንድ ቦታዎች አንፃራዊ ሰላም አግኝተው የመማር ማስተማር ሂደቱን የጀመሩ ሲኖሩ የተወሰኑት ደግሞ በሰላም እጦቱ ቀጥለዋል፡፡
ነገር ግን አንፃራዊ ሰላም ኖሯቸው የመማር ማስተማሩን ሂደት ቢጀምሩም ተማሪ በሚፈለገው ልክ ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ አይደሉም፡፡
ወደ ገበታቸው የተመለሱትም ቢሆኑ ባለፉበት ችግር ምክንያት ጭንቀት ውስጥ የገቡ እና በአግባቡ ትምህርታቸውን የማይከታተሉ ተማሪዎች ጥቂት አይደሉም፡፡
ተማሪዎቹ ወደ ቀደመው የትምህርት አቀባላቸው እንዲመለሱ፣ የመማር ማስተማሩም በተገቢው መንገድ እንዲሄድ በጦርነት ላይ የነበሩ አሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱት ተማሪዎች እንዴት ይታገዙ?
ፋሲካ ሙሉወርቅ ያሰናዳችውን በፍቅሩ አምባቸው
Comments