TRACK
የኢትዮጵያ 97 በመቶ ገቢና ወጭዋ ወይም አጠቃላይ ንግዷ “በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር “ የሚተላለፍ በመሆኑ ይህ መስመር በብርቱ መጠናከር አለበት ተባለ
00:00
ሐምሌ 25 2017
የኢትዮጵያ 97 በመቶ ገቢና ወጭዋ ወይም አጠቃላይ ንግዷ “በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር “ የሚተላለፍ በመሆኑ ይህ መስመር በብርቱ መጠናከር አለበት ተባለ።
ይህን የተናገሩት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ናቸው።
ገዥው ኤክፖርትን ማበረታታት ከፈለግን ወደ ኋላ የቀረውን የሎጀስቲክስ ስራ ቅድሚያ ማሻሻል አለብን ብለዋል።
የሎጀስቲክስ ችግሩን በሥርዓቱ ማስተካከል ማለትም ፤ የፋይናንስ ሥርዓቱን ዘመናዊ ማድረግ ነው፤ ኤክስፖርቱን ማሻሻል ማለትም የውጭ ምንዛሪውን ለውጦ የፋይናንስ ሥርዓቱንም ከፍ ማድረግ ነው ሲሉ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል።
Comments
00:00
awesome. keep it up. have a great weekend. Amen/Allah. greetings from south africa