የራዳር መሳሪያ  እጥረት ለስራው ፈተና እንደሆነበት የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተናገረ
TRACK

የራዳር መሳሪያ እጥረት ለስራው ፈተና እንደሆነበት የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተናገረ

Avatar

የካቲት 13፣2016

የተሽከርካሪዎችን የፍጥነት ወሰን ለመቆጣጠር የሚያግዘውን የራዳር መሳሪያ እጥረት ለስራው ፈተና እንደሆነበት የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተናገረ፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሸገር እንደተናገረው የትራፊክ አደጋን ከሚፈጥሩ ምክንያቶች መካከል ቀዳሚው ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እንደሆነ ይነገራል፡፡

ባለበት የሰው ሃይል እና የራዳር መሳሪያዎች እጥረት ምክንያት የፍጥነት ወሰን ቁጥጥር የሚሰራው አልፎ አልፎ መሆኑን የተናገሩት በባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የዲጂታል ሚዲያ ባለሞያ የሆኑት አቶ መኳንንት ምናሴ ናቸው፡፡

ከሰሞኑ በሁለት ክፍለ ከተሞች ለ2 ሰዓታት ብቻ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከ325 በላይ ሰዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክሩ ተገኝተው እርምጃም ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡

የፍጥነት ወሰን የቁጥጥር ባለሞያዎች በሌሉባቸው አካባቢዎች፤ አሽከርካሪዎች በአብዛኛው በፍጥነት እንደሚያሽከረክሩ የነገሩን አቶ መኳንንት ያለብንን የሰው ሃይል እጥረትን ለመቅረፍ በቅርቡ 400 ሰራተኞችን ለመቅጠር ተሰናድተናል እንዲሁም የመንገድ ካሜራዎችን በመግጠም ለመቆጣጠር አስበናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምንታምር ፀጋው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የፍጥነት_ወሰን # የትራፊክ_አደጋ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar