TRACK
በአዲስ አበባ የድንገተኛ አደጋ ህክምና በሚሰጡ የጤና ተቋማት ለመታከም ከሚመጡት ውስጥ 36 በመቶ በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው የሚመጡ ናቸው ተባለ፡፡
00:00
ታህሳስ 23፣2017
በአዲስ አበባ የድንገተኛ አደጋ ህክምና በሚሰጡ የጤና ተቋማት ለመታከም ከሚመጡት ውስጥ 36 በመቶ በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው የሚመጡ ናቸው ተባለ፡፡
የትራፊክ አደጋ ከተከሰተ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ለማግኘትም ብዙዎች እንደሚቸገሩ ተነግሯል፡፡
በዚህም ምክንያት የትራፊክ አደጋ ከደረሰ በኋላ በቅራቢያ ወደሚገኙ የጤና ተቋማት ሳይሄዱ ጉዳቱ ተባብሶ እንደ ጥቁር አንበሳ ወዳሉና የድንገተኛ ህክምና የሚሰጡ የመንግስት የጤና ተቋማት የሚመጡ ብዙዎች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡
የመንገድ ደህንነቱን የሚያሻሽሉ ስራዎች ለመከወን ከአደጋ በኋላ ያለውን የህክምና አገልግሎት ለማሻሻል የሚከወኑ መሆኑን የተናገሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ናቸው፡፡
ከተከሰቱ የተለያዩ አደጋዎች ውስጥ 36 በመቶ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጐጂ የሆኑ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ የሚሉት አቶ ክበበው፤ ከዚህ ውስጥ ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል እንደ ሀገር አዲስ አበባ ያለው የመንገድ ትራፊክ አደጋዎች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል ብለዋል፡፡
Comments
00:00