TRACK
የአላባ አንጋጫ ዋቶ የመንገድ ፕሮጀክትን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የኮንትራት ውሉ እንዲከለስለት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጠየቀ
ግንቦት 26 2017
የአላባ አንጋጫ ዋቶ የመንገድ ፕሮጀክትን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አሁን ባለው የዋጋ ግሽበት ተሰልቶ የኮንትራት ውሉ እንዲከለስለት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጠየቀ፡፡
ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ መጠናቀቅ የነበረበት የመንገድ ፕሮጀክቱ አስካሁን አፈፃፀሙ 23 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ አማካሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ተቋራጩ በአግባቡ እና በእቅድ ባለመስራቱ ፕሮጀክቱ በመጠናቀቅያ እድሜው 77 በመቶው አልተሰራም ብሏል፡፡
መንገድ ፕሮጀክቱ እስካሁን የአስፓልት ንጣፍ 7 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
Comments