መጋቢት 4 2017
በኢትዮጵያ የፍላጎቱን ያህል አለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟሉ በቂ የሂሳብ ባለሞያዎች እንደሌሉ ተነገረ፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡
ኢንስቲትዩቱ አለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟሉ ብቁ የሂሳብ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው መባሉን ተከትሎ ስለ አስፈላጊነቱ ከምክር ቤት አባላት ጥያቄ ተነስቷል፡፡
የስልጠና ተቋም ከሆነ ኢንስቲትዩት በማቋቋም የመንግስትን ወጪ ከመጨመር ይልቅ ስራው ለምን በትምህርት ሚኒስቴር በኩል አልተሰራም የሚል ጥያቄ ከፓርላማ አባላት ተጠይቋል፡፡
Comments
500 የሚያሀሉ ወደ ዉጪ ከምትልኩ እነሱን እዚህ አምጥተችሁ ቢታሰለጥኑን ጥሩ ነበር፡፡