ህዳር 1 2018
ምርቶች በወጣላቸው ደረጃ መሰረት ተዘጋጅተው ለገበያ መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገው የቁጥጥር የላላ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
መረጃዎችን የሚያጸድቀው ቦርድ የሚወጡ ደረጃዎችን አተገባበር በየጊዜው እንዲከታተል የሚያስችል አዲስ አሰራር ሊከተል እንደሆነም ሠምተናል፡፡
በሌላ በኩል ለሁለት ተጨማሪ ሀገር በቀል ምግብ ነክ ምርቶች በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ደረጃ መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ምግብ ነክ ለሆኑ ስድስት አገር በቀል ምርቶች ደረጃ ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡
ሽሮ፣ በርበሬ፣ ቆሎ፣ በሶ፣ አረቄ እና ጠጅ ደረጃው የተዘጋጀላቸው ምርቶች ናቸው፡፡
ለምርቶቹ የወጣውን ደረጃ ህብረተሰቡ እንዲያውቀው እንዲሁም የተመረጡ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ደረጃውን መሰረት አድርገው ምርቱን እንዲያዘጋጁ መደረጉን በኢንስቲትዩቱ የደረጃ ዝግጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግስቱ ነግረውናል፡፡
Comments