መጋቢት 4 2017
በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ዓይነ ስውርነት በግላኮማ የሚመጣው ቀዳሚው መሆኑ ተነገረ፡፡
ግላኮማ ሲከሰት ለረጅም ጊዜ ምልክት ለማሳየቱ ብዙዎችን ላይነ ስውርነት እየዳረገ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ዓለም አቀፍ የግላኮማ ሳምንት በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየታሰበ ነው፡፡
በግላኮማ ምክንያት የሚደርሰውን የዓይን ብርሃን ማጣት ለመከላከልም የዓይን ግፊትን በየጊዜው መከታተል እና ምርመራ ማድረግ ይገባል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በቅርብ የተሰራ ጥናት ባይኖርም ከ 19 ዓመት በፊት በነበረው መረጃ በሌሎችም ምክንያቶች የሚፈጠር ዓይነት ስውርነት ውስጥ በግላኮማ የሚከሰተው ቀዳሚ መሆኑን የነገሩን የዓይን ሀኪም እና የግላኮማ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ናሆም አያሌው ናቸው፡፡
አሁን ባለው መረጃ በአለም ደረጃ 80 ሚሊዮን የሚያክል ህዝብ ወይም ሰው በግላኮማ ተጠቂ እንደሆነ ያሳያል፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት ላይ ግላኮማ በስፋት እንደሚታይ የሚናገሩት ዶክተር ናሆም ከአንድ ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 10 ሺህ ያህሉ በግላኮማ እንደሚያዙ ጥናት ያሳያል ይላሉ፡፡
Comments