በየጊዜው መንግስት ታሪፍ ያወጣላቸው ሸቀጦች በነጋዴዎች ፍላጎት ብቻ ዋጋቸው ይጨምራል፡፡
TRACK

በየጊዜው መንግስት ታሪፍ ያወጣላቸው ሸቀጦች በነጋዴዎች ፍላጎት ብቻ ዋጋቸው ይጨምራል፡፡

Avatar

ግንቦት 11/2018

በየጊዜው መንግስት ታሪፍ ያወጣላቸው ሸቀጦች በነጋዴዎች ፍላጎት ብቻ ዋጋቸው ይጨምራል፡፡

አንዳንዶችም እየደበቁት በከፍተኛ ዋጋ ይሸጣሉ፡፡

ከተመን በላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ይጨምራል፤ የሸቀጦች ዋጋም በትናንትናው ልክ ዛሬ አይገኝም።

ጭማሪው ምጣኔ ሐብታዊ ምክንያት የለውም፡፡ ሸማቹም ለምን ብሎ የመጠየቅ ልምድ የለውም፡፡

"ለምን" ብለው የሚጠይቁ ሲኖሩም ጭማሪውን አሜን ብለው የተቀበሉ ተደርበው ሲያዋክቡ ይታያሉ፡፡

ለነጋዴዎቹ ህገወጥነት ፍላጎት የሸማቹ ዝምታ እና የተባለውን "አሜን" ብሎ መቀበል በገበያው ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ አለው? ስንል የጠየቅናቸዉ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ዶ/ር) "በኢኮኖሚክስ ህግ ሸማቹ የገበያው ንጉስ ነው። ነገር ግን ሸማቹ 'ለምን?' ብሎ ካልጠየቀና ያለአግባብ የሚደረጉ ጭማሪዎችን በዝምታ ካስተናገደ፣ ነጋዴው ያሻውን ዋጋ እንዲጭን እድል ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ የገበያ መዛባትን ይፈጥራል ብለዋል።

ስለዚህ ዜጎች በህብረት ሆነው መጠየቅ ይኖርባቸዋል ሲሉ ይመክራሉ።

Comments

Avatar