ወደ ህክምና ተቋማት የአጥንት ህክምና ፈልገው ከሚመጡ ተገልጋዮች አብዛኛዎቹ በትራፊክ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ተባለ፡፡
ታህሳስ 20/2018
ወደ ህክምና ተቋማት የአጥንት ህክምና ፈልገው ከሚመጡ ተገልጋዮች አብዛኛዎቹ በትራፊክ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ተባለ፡፡
የትራፊክ አደጋ አሁንም ከሌሎች ጉዳቶች ይልቅ ለአጥንትና መገጣጠሚያ ችግሮች ቀዳሚ መንስኤ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል ጉዳቱ ከባድ ቢሆንም የህክምና ወጪው ከፍተኛ መሆንና ህክምናው በሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማት አለመገኘቱም ተጨማሪ ጫና መፍጠሩንም የኢትዮጵያ የአጥንት ቀዶ ህክምና ማህበር ተናግሯል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንትና የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ኤፍሬም ገብረ ሐና እንደሚናገሩት ከአጥንት ጉዳት ጋር በተያያዘ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው የትራፊክ አደጋ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እስካሁን የጉዳት መረጃ መመዝገቢያ ቋት የሌላት በመሆኑም በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ አድርጎታል የሚሉት ዶ/ር ኤፍሬም የኢትዮጵያ የአጥንት ቀዶ ህክምና ማህበር በራሱ ይህንን ለመስራት የጀመራቸው ስራዎች አሉ ብለዋል፡፡
አደጋዎች እንዴት ነው የሚከሰቱት? የት ነው በብዛት ያሉት? የሚለውን ለመለየት የአደጋ መመዝገቢያ የለም ያሉት ዶ/ር ኤፍሬም እዚህም ላይ ለመስራት እንደማህበር የያዘው አንድ ትልቅ እቅድ አለ አዋሣ ላይ በሙከራ ደረጃ የአደጋ መረጃ መመዝገቢያ አስጀምረናል ብለዋል፡፡
ከአጥንት ጋር የተያያዙ ህክምናዎች በተለይም በአደጋ ምክንያት የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ውጪ የሚጠይቅ ለህክምና የሚሆኑ ግብዓቶችም ውድ መሆናቸው ህክምናው ላይ ተጽእኖ አለው የሚሉ��� ዶክተር ኤፍሬም የህክምና ውጪው ጥቂትም ቢሆን በጤና ኢንሹራንስ ውስጥ ተካቶ እንዲሰራበት ማህበሩ ግፊት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Comments