ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ‘’ከዚህ ባንክ ነው የደወልነው’’ በሚል በተለያየ ዘዴ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብን የሚዘርፉ አጭበርባሪዎች እየበረከቱ ነው
TRACK

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ‘’ከዚህ ባንክ ነው የደወልነው’’ በሚል በተለያየ ዘዴ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብን የሚዘርፉ አጭበርባሪዎች እየበረከቱ ነው

00:00

ህዳር 12፣2017

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ‘’ከዚህ ባንክ ነው የደወልነው’’ በሚል በተለያየ ዘዴ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብን የሚዘርፉ አጭበርባሪዎች እየበረከቱ ነው፡፡

በዚህ መንገድ በአጭበርባሪዎች ከ100 ሺህ እስከ ሚሊዮኖችን ብር የባንክ ተቀማጭ ገንዘባቸውን የተዘረፉ መኖራቸውን ሰምተናል፡፡

እኛም ለዘረፋ ሙከራ ተደውሎልን በመቅረፀ ድምፃችን ያስቀረነውን ለጥንቃቄ ይሆናችሁ ዘንድ አሰናድተነዋል፡፡

ከደዋዩ ድምፅ እንምትረዱት በመጨረሻ ገንዘባችሁን የምታስላልፉበትን የአካውንት ቁጥር እና የሚገባለትን ሰው ስም ጭምር እስከ አያቱ ይናገራል፡፡

ነገር ግን ብሩ ወደ እሱ እንደሚተላለፍ በፍፁም አይነግራችሁም፡፡

ስለ ጉዳዩ የጠቅነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉ እየበዛ መምጣቱን ተናግሯል፡፡

Comments

00:00