በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ60,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተነገረ
TRACK

በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ60,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተነገረ

Avatar

ጥቅምት 14፣2017

በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ሥርጭት ሰፍቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ60,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተነገረ፡፡

ይህንን የተናገረው የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው፡፡

ከሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ600,000 በላይ ሰዎች በወባ የተያዙ መሆናቸውን ሪፖርት ያሳያል ብሏል ኢንስቲትዩቱ፡፡

የአዊ ዞን፣ የደቡብ ጎንደር ዞን፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ የምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በቅደም ተከተላቸው ወረርሽኙ ከፍተኛ ስርጭት የሚታዩባቸው አካባቢዎች ናቸው ተብሏል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር አሁን በክልሉ ያለው የወባ ወረርሽኝ ካለፉት 5 ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱን ይናገራሉ፡፡

Comments

Avatar