TRACK
2017 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚሰጧቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እውቅና መስጠት እጀምራለሁ ሲል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተናገረ
መስከረም 3፣2017
2017 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚሰጧቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እውቅና መስጠት እጀምራለሁ ሲል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተናገረ።
ባለስልጣኑ ይህንን ያለው አድማስ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው 16ተኛው አለም አቀፍ አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ነው።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚነሳውን የትምህርት ጥራት መጓደል ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን የተናገረው ባለስልጣኑ ተቋማትን እንደገና መዝግቦ በጥራት እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና አሰራር ሲያወጣ ሁለት አመት ማስቆጠሩን ተናግሯል።
ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር በተመዘገቡበት የትምህርት ዘርፍ ማስተማር ይችላሉ ውይ የሚለው ብቻ ታይቶ ፈቃድ ይሰጣቸው እንደነበረ የተነገረ ሲሆን በአዲሱ የጥራት መመዘኛ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን የጥራት ደረጃ ማሟላታቸው እየተመዘነ ዳግም እንዲመዘገቡ ይደረጋል መባሉን ሰምተናል፡፡
Comments