''በትምህርት ፖሊሲዎች ዙሪያ ጥናት አድርገን ለፓርላማ አቅርበን ፓርላማውም ከተቀበለን በኋላ ምንም ታሳቢ ሳያደርጋቸው ወደ ጎን ትቷቸዋል'' ማህበሩ
TRACK

''በትምህርት ፖሊሲዎች ዙሪያ ጥናት አድርገን ለፓርላማ አቅርበን ፓርላማውም ከተቀበለን በኋላ ምንም ታሳቢ ሳያደርጋቸው ወደ ጎን ትቷቸዋል'' ማህበሩ

Avatar

ህዳር 3፣ 2017

መንግስት፤ በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎች ዙርያ ግብዓቶችን እንዳቀርብ ይጠይቀኝና ያቀረብኳቸው ግብዓቶች ግን በቅጡ ሳያያቸው ውድቅ ያደርጋቸዋል ሲል የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ የትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር ተናገረ፡፡

ማህበሩ በተለያዩ ጊዜያት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል በሚወጡ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ላይ ያለውን አተያይ እና የመፍትሄ ሀሳቦች ጥናት አድርጎ እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡

ነገር ግን እነዚህን በመንግስት ተጠይቆም ሆነ በራሱ ተነሳሽነት የሚያቀርባቸው ግብዓቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች በአግባቡ እንኳ ታይተው አያውቁም ሲል ማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ሲናገር ሰምተናል፡፡

የማህበሩ ፕሬዚደንት አረጋ ይረዳው(ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎች ዙሪያ ዘርፉን አይተን እና ጥናት አድርገን ለፓርላማ አቅርበን ፓርላማውም ከተቀበለን በኋላ ምንም ታሳቢ ሳያደርጋቸው ወደ ጎን ትቷቸዋል ብለዋል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments

Avatar