ሚያዝያ 20 2017
በትግራይ ክልል የተጋነነ የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ተዘዋውሮ ለመስራት መቸገሩን የእምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅጫፍ ፅህፈት ቤት ተናገረ፡፡
ከተቋሙ እንደሰማነው በጥቁር ገበያ ነዳጅ ከመደበኛ ዋጋው እስከ ሁለት እጥፍ ይሸጣል፤ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ነዋሪው ለመንቀሳቀስ ተቸግሯል ተብሏል፡፡
በትግራይ ክልል ያለው የነዳጅ እጥረት እየተባባሰ መምጣቱን የሚናገረው ፅህፈት ቤቱ ይህ ችግር በክልሉ ተዘዋውሮ ለመስራት እንቅፋት ሆኖብኛል ብሎናል፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ ባሉ ማደያዎች ነዳድ ማግኘት ብር እሆነ ነው፤ነዳጅ ሰወር ብሎ በጥቁር ገበያ ከመደበኛ ዋጋው እስከ ሁለት እጥፍ እየተሸጠ ነው፤የትራንስፖርት ዋጋውም በዚያው የሚጠየቀው ከነበረው በ1እና2 እጥፍ ሆኗል፤ እኛ የፌድራል ተቋም እንደመሆናችን ሂሳብ የምናወራርደው በመደበኛ ዋጋው ነው፤ የግድ ስራውን መስራት ስላለብን ለትራንስፖርት የምናወታው በእጥፍ ነው ያሉን የቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ እምባዬ ናቸው፡፡
Comments