‘’ግዕዝ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል’’ አሜሪካ ከሚገኙ  2 የትምህርት ተቋማት በመተባበር ኢትዮጵያዊያን ትምህርት እንዲያገኙ የሚያደርግ ስምምነት አደረገ
TRACK

‘’ግዕዝ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል’’ አሜሪካ ከሚገኙ 2 የትምህርት ተቋማት በመተባበር ኢትዮጵያዊያን ትምህርት እንዲያገኙ የሚያደርግ ስምምነት አደረገ

00:00

ታህሳስ 23፣2017

‘’ግዕዝ የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል’’ አሜሪካ ሀገር ከሚገኙ ሁለት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያዊያን ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ የሚያደርግ ስምምነት አደረገ፡፡

ግዕዝ ስምምነት ያሰረው ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (California State University) እና ግሎባል አካዳሚ ኦፍ ፋይናንስ ኤንድ ማጅመንት (Global Academy of finance & Management) ጋር ነው፡፡

ሁለቱን ተቋሞች ውክልና ይዞ ከግዕዝ ጋር የተፈራረመው ደግሞ በአሜሪካን ሀገር በኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ቃልሄር ሃብ (Kalherhub) ነው፡፡

ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገው ስምምነት ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሶስተኛ (PhD) ድረስ በአካል አሜሪካ ሂደው ወይም በኦላይንልት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል መሆኑንን የGEEZ EDUCATION & training ተቋም መስራቾችና ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ዘሚካኤል ተናግረዋል፡፡

Comments

00:00