ጥቅምት 21 2018
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው እውነተኛ እርቅ እና ሰላም እንዲወርድ የንግዱ ማህበረሰብ ጠየቀ፡፡
ነጋዴዎቹ ይህን የጠየቁት ትናንት "የንግድ ሚና ለሰላም ግንባታ'' በሚል ሀሳብ አዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባሰናዳው የፓናል ወይይት ላይ ነው።
የውይይቱ ተሳታፊ አደም ካሚል (ረ/ፕ) ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የረዥም ጊዜ ታሪኳ ፍትህ እና ሰላም እንደሆነ አስረድተዋል።
ያ ባይሆን ኖሮ ነብዩ ሞሀመድ ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ አይልኩም ነበር ይህም የምንኮራበት ታሪክ ነው ሲሉ አስታውሰዋል።
ትናንት የፍትህ እና የሰላም ሀገር ከሆነች ዛሬ ምን ተፈጥሮ ነው? ችግሩ ምንድነው? የሚለውን ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች ትኩረት አድርገው በጥናት ሊለዩት ይገባል ብለዋል።
ሌላ የውይይቱ ተሳታፊ መሳሪያ አንስተው እየታገሉ ያሉት የእኛው እህት ወንድሞቻችን ናቸው በስልጣን ላይ ያሉትም እንደዛው የእኛው ናቸው እያፋጁን ያሉት ሃያላን ሀገሮች መሳሪያ እየሸጡልን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
“ችግራችንን ለምንድነው በክብ ጠረጴዛ የማንፈታው? ሲሉ የጠየቁት ተሳታፊው መሳሪያ አምራች ሀገሮች ለአፍሪካዊያን እና ኋላቀር ሀገሮች መሳሪያ እየሸጡ ነው ይህም ለራሳቸው ለመበልፀግ እንዲሁም የእነሱ አሽከሮች ሆነን እንድንኖር ነው’’ ሲሉ ተናግረዋል።
Comments